إِنَّا فَتَحْنَا لَكَ فَتْحًۭا مُّبِينًۭا
እኛ ላንተ ግልጽ የኾነን መክፈት ከፈትንልህ፡፡
ሱራ 48 · መዲናዊ
ድሉ · 29 አንቀጾች
إِنَّا فَتَحْنَا لَكَ فَتْحًۭا مُّبِينًۭا
እኛ ላንተ ግልጽ የኾነን መክፈት ከፈትንልህ፡፡
لِّيَغْفِرَ لَكَ ٱللَّهُ مَا تَقَدَّمَ مِن ذَنۢبِكَ وَمَا تَأَخَّرَ وَيُتِمَّ نِعْمَتَهُۥ عَلَيْكَ وَيَهْدِيَكَ صِرَٰطًۭا مُّسْتَقِيمًۭا
አላህ ከኃጢአትህ ያለፈውንና የሚመጣውን ላንተ ሊምር ጸጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላ ቀጥተኛውንም መንገድ ሊመራህ (ከፈተልህ)፡፡
وَيَنصُرَكَ ٱللَّهُ نَصْرًا عَزِيزًا
አላህ ብርቱን እርዳታ ሊረዳህም (ከፈተልህ)፡፡
هُوَ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ ٱلسَّكِينَةَ فِى قُلُوبِ ٱلْمُؤْمِنِينَ لِيَزْدَادُوٓا۟ إِيمَٰنًۭا مَّعَ إِيمَٰنِهِمْ ۗ وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًۭا
እርሱ ያ በምእምናን ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው፡፡ ለአላህም የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አልሉት፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
لِّيُدْخِلَ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتِ جَنَّٰتٍۢ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَيُكَفِّرَ عَنْهُمْ سَيِّـَٔاتِهِمْ ۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عِندَ ٱللَّهِ فَوْزًا عَظِيمًۭا
ምእምናንንና ምእምናትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ሊያገባቸው ከነርሱም ኃጢአቶቻቸውን ሊያብስላቸው (በትግል አዘዛቸው)፡፡ ይህም ከአላህ ዘንድ የኾነ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
وَيُعَذِّبَ ٱلْمُنَٰفِقِينَ وَٱلْمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلْمُشْرِكِينَ وَٱلْمُشْرِكَٰتِ ٱلظَّآنِّينَ بِٱللَّهِ ظَنَّ ٱلسَّوْءِ ۚ عَلَيْهِمْ دَآئِرَةُ ٱلسَّوْءِ ۖ وَغَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيْهِمْ وَلَعَنَهُمْ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَهَنَّمَ ۖ وَسَآءَتْ مَصِيرًۭا
በአላህም ክፉ ጥርጣሬን ተጠራጣሪዎቹን መናፍቃንና መናፍቃትን፣ ወንዶች አጋሪዎቻችንና ሴቶች አጋሪዎችንም ያሰቃይ ዘንድ (በትግል አዘዘ)፡፡ በእነርሱ ላይ ክፉ ከባቢ አለባቸው፡፡ በእነርሱም ላይ አላህ ተቆጣባቸው፡፡ ረገማቸውም፡፡ ለእነርሱም ገሀነምን አዘጋጀላቸው፡፡ መመለሻነትዋም ከፋች፡፡
وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا
ለአላህም የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አልሉት፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡
إِنَّآ أَرْسَلْنَٰكَ شَٰهِدًۭا وَمُبَشِّرًۭا وَنَذِيرًۭا
እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን በእርግጥ ላክንህ፡፡
لِّتُؤْمِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُ وَتُسَبِّحُوهُ بُكْرَةًۭ وَأَصِيلًا
በአላህ ልታምኑ፣ በመልክተኛውም (ልታምኑ)፣ ልትረዱትም፣ ልታከብሩትም፣ (አላህን) በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱትም (ላክነው)፡፡
إِنَّ ٱلَّذِينَ يُبَايِعُونَكَ إِنَّمَا يُبَايِعُونَ ٱللَّهَ يَدُ ٱللَّهِ فَوْقَ أَيْدِيهِمْ ۚ فَمَن نَّكَثَ فَإِنَّمَا يَنكُثُ عَلَىٰ نَفْسِهِۦ ۖ وَمَنْ أَوْفَىٰ بِمَا عَٰهَدَ عَلَيْهُ ٱللَّهَ فَسَيُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًۭا
እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው፡፡ የአላህ እጅ (ኀይሉ) ከእጆቻቸው በላይ ነው፡፡ ያፈረሰም ሰው የሚያፈርሰው በነፍሱ ላይ ብቻ ነው፡፡ በእርሱ ላይ አላህን ቃል ኪዳን የተጋባበትን የሞላም ሰው ታላቅ ምንዳን በእርግጥ ይሰጠዋል፡፡